ማህበር ኣቡነ ሰላማ ወርሃዊ ክብረ ብዓል ስለሴ እና ሃና ወእያቄም በደመቀ ሁኔታ ኣከበረ

ማህበር ኣቡነ ሰላም ከ እላማዎቹ ኣንደ የሆነው የድንል ማርያምን ፡የጌታችንና መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ፣ ቅዱስን ፣ሰማእታት ፣መላእክት ወርሃዊ ይሁን ኣማታዊ ክብረ ባዓላቸዉን በማክበር በረከታቸዉን መካፈል እንድሁነ የታወቀ ሁኖ ትላንትና 7/2/2006 በግዕዝ የሃና እያቂም እና የሰላሴን ድርብ ክብረ በዓል በደመቀ ሁኔታ ኣክብሮ ዋለ ።

ቦዓሉ በኣባታችን እና መምህራችን ኣባ ሳሙኤል ቡራኬ ጸሎት ከተከፈተ ቦሃላ በዘማርያን ማህበር ኣቡነ ሰላማ ለብዓሉ የሚመለከት መዝሙሮችን በመዘመር ለብዓሉ ድምቀት ትልቅ ኣስተዋጽኦ ኣድርገው ዋሉ ፣ከዛም በመቀጠል ኣባታችን እና መምህራችን ኣባ ሳሙኤል ከ(ማት 17፡20)ያለው ሃይለ ቃል በመጠቀም ለብ የሚመስጥ ቃለ ወንጌል ለመእመን ኣስተማሩ ።

ቀጥሎም በብዓሉ ምክናይት የተዘጋጀዉን ጸበል መእመናን ከቀመሱ በሆላ በዘማርያን ማሕበር ኣቡነ ሰላማ መዝሙሮች ኣከታትለው ኣቀርቡ ፣መእመኑም በኣገኘው በረከት እየተደሰተ ጉባኤዉን ኣባታችን በጸሎት ዘጉት።