christmas star Mahbere Abune Selama- self help association, support those in need, Spiritual gatherings, youth and adult counselling  christmas star

lo 1

Latest news/ የቅርብ ዜናዎች

View more featured blog entries
  • Home
    Home This is where you can find all the blog posts throughout the site.
  • Archives
    Archives Contains a list of blog posts that were created previously.
Super User

Super User

Super User has not set their biography yet

ማህበር ኣቡነ ሰላማ ወርሃዊ ክብረ ብዓል ስለሴ እና ሃና ወእያቄም በደመቀ ሁኔታ ኣከበረ

ማህበር ኣቡነ ሰላም ከ እላማዎቹ ኣንደ የሆነው የድንል ማርያምን ፡የጌታችንና መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ፣ ቅዱስን ፣ሰማእታት ፣መላእክት ወርሃዊ ይሁን ኣማታዊ ክብረ ባዓላቸዉን በማክበር በረከታቸዉን መካፈል እንድሁነ የታወቀ ሁኖ ትላንትና 7/2/2006 በግዕዝ የሃና እያቂም እና የሰላሴን ድርብ ክብረ በዓል በደመቀ ሁኔታ ኣክብሮ ዋለ ።

ቦዓሉ በኣባታችን እና መምህራችን ኣባ ሳሙኤል ቡራኬ ጸሎት ከተከፈተ ቦሃላ በዘማርያን ማህበር ኣቡነ ሰላማ ለብዓሉ የሚመለከት መዝሙሮችን በመዘመር ለብዓሉ ድምቀት ትልቅ ኣስተዋጽኦ ኣድርገው ዋሉ ፣ከዛም በመቀጠል ኣባታችን እና መምህራችን ኣባ ሳሙኤል ከ(ማት 17፡20)ያለው ሃይለ ቃል በመጠቀም ለብ የሚመስጥ ቃለ ወንጌል ለመእመን ኣስተማሩ ።

ቀጥሎም በብዓሉ ምክናይት የተዘጋጀዉን ጸበል መእመናን ከቀመሱ በሆላ በዘማርያን ማሕበር ኣቡነ ሰላማ መዝሙሮች ኣከታትለው ኣቀርቡ ፣መእመኑም በኣገኘው በረከት እየተደሰተ ጉባኤዉን ኣባታችን በጸሎት ዘጉት።

ማህበር ኣቡነ ሰላማ ከግዜ ወደ ግዜ ህላውነቱን ኣስመሰከረ

         ማህበር ኣቡነ ሰላም ከሳቴ ብርሃን በታሪክ እንደሚታወቀው ከሚመሰረት ኣስይዞ ኣስካሁን ተፈታኝ ማህበር መሆኑን ታሪክ ማህበር ኣቡነ ሰላማ ተዘግቦ ይገኛል ።    

ዶክሜንት ማህበር ኣቡነ ሰላማ እንድሚገልጠው ለዚህ ማህበር ፈተና የሚያበዙበት በውጭ ኣንድ ኣንድ የቤተክርስትያን ኣገልጋዮች ነን ባዮች ግን ድብቅ መጥፎ ስራ ያላቸው ፣መናፍቃን፣ኣንድ ኣንድ ማህበሮች በዘረኝነትና በወገንነት የተጠቁ ፣እንዲሁም የፖለቲካ ሰዎች ሲሆኑ ፡ምክንያታቸው ደግሞ እናዛ ኣገልጋዮች በድብቅ የሰይጣን ስራ እንደ ደበተራ የመሳሰሉ ስራዎች የሚሰሩ ኮሆኑ  ማህበሩ ( ኣቡነ ሰላማ )ስለምያጋልጣቸው ወይም ስለ ማይቀበላቸው፣መናፍቃን ማህበረ ኣቡነ ሰላማ ጸረ መናፍቃን ስለሆነ ። የፖለቲካ ሰዎች ደግሞ የበዛ የማህበሩ ኣባል ወጣት በመሆኑ ከእግዚኣብሄር ኣገልጋይ የፖለቲካ ኣገልጋይ የማድረግ ህልም ስላላቸው ነው።

         በውስጥ በማህበሩ ሁኖ ፈተና የምያመጡት ደግሞ የዘረኝነት ባህርያቸው ያልጠፋላቸው፣ለስማቸው የሚቆሙ፣ ተርፍ የሚፈለጉ ወይም የግንዘብ ፍቅር ያላቸው ነው።

   በእንድዚህ እያለ መሰራቷን ጌታችንን መድሃኒታችን እየሱሱ ክርስቶስን ኣድራጋ የምትጓዝ ማህበር ኣቡነ ሰላማ ፈተና እንኳን ቢበዛ በእግዚኣብሄር ስልጣን በድንግል ማርያም ኣማላጅነት በኣባ ሰላማ ቃል ኪዳን እሳካሁን ፈተናዉን እያለፈች ህላውነቷን እያረጋገጠች ትገኛለች ፣

ኣሁንም ባለፈው ሳምንት እራሳቸዉን ኣመሳሰልው በማህበሩ ወስጥ ሲያገለሉ የቆዩ ኣባሎች የዘረኘነትና የስልጣን ጥማቸዉን ለማርካት በውስጥ በሴራ ማህበር ለማፍረስ ከሚንቀሳቀሱ ሌሎች ቡድኖች ጋር ሲንቀሳቀሱ ቆይተው ባለፈው ሳምንት ግን ግዜው ደርሶዋል ብለው ብኣደባባይ ኣውጥተው ማህበሩን ለመከፋፈል ያደረጉት ሙከራ እራሳቸው በቻ ሰልባ ሁነዋል ።ስለዚ ጉዳይ ባደርጉት የማህበሩ ጠቅላላ ሰብሰባ ሁሉ ኣባል ለክ ቆፎው ይትነካ ንብ በመምሰል ድምጻቸዉን ኣስመተዋል በዛ ሰብሰባ እንደተገመገመው ማህበር ኣቡነ ሰላማ ከጌዜ ወድግዜ እየበለጸገና ፍቅሩን እያዳበረ እንጂ በሚመጣ ፈተና ሁሉ ተደናግጦ ቁልፉን የሚፈታ እዳልሆነ ኣረጋገጦዋል።በዚ ሙከራ ያልተሳካላቸው ወገኖች ኣሁንም እንደሌሎች በኣሉባልታ ወሬ ማህበሩ ፈረሰ ተበተን እያሉ የሰውን ጭንቅላት እያዞሩ እንዲሁም ሰኔ ጎልጎልታንና የቅዱስ ሚካኤልን ድርሳን ከኣንገታቸው እያወጡ በማቃጠል መናፍቅነታቸዉን ስለኣረጋገጡ ማህበር ኣቡነ ሰላማ ብሙሉ ድምጽ ኣሰናብቶቾዋል  ፡በዚ ኣጋጣሚ ማህበር ኣቡነ ሰላማ እንዃን ሊፈርስ ከነበራው በበለጠ ፍቅሩን እና ኣገልግሎቱን ኣሳድሶ፡በጣም ኣስደናቂ በሆነ እደግት እየቀጠለ መሆኑን እናረጋግጣለን።

በዚህ ምክንያት ኣባታችን መምህራችን ኣባ ሳሙኤል (ከ ያዕቆብ 1፡12)መርኩስ ኣድርገው በሰጡት ትምህርት እግዚኣብሄር ለጠላታችን እዲፈተነን የፍቅድለት ይሆናል እንዲበተነን ግን በፍጹም ፣እንድያዉም ፈተና ከሌለ ጸጋ ስሌለ ፈተናን በኣኮቴት መቀበል እንዳለብን ገለጡ ።

ማህበር ኣቡነ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን ገዳሞችን መርዳት እየቀጠለ ነው

ማህበረ ኣቡነ ሰላማ ከዕላማዎቹ ኣንዱ ገዳሞቹን ያላቸዉን ችገር በማጥናት ማገዝ የሚል ነው በዚህም ምክንያት ኣስካሁን በተላያየ ግዜና ቦታ ለተለያዩ ገዳሞች የገንዘብ እርዳታ ሲያደርግ ቆይቶዋል ።

ኣሁንም ማህብረ ኣቡነ ሰላማ “ውሻ ቢጮህም ግምል ጉዞዉን ኣይቛርጥም “እንድሚባለው የተለያዩ የማህበሩ ጠላቶች ማህበሩን ለማፍረስ በሚንቀሳቀሱበት ሰዓት የተለያዩ ወዳጆችን በማትረፍ የማህበሩን ኣገልግሎት ተጣቃሚ ለመሆን በቅቶዋል ። እስራኤል እየሩሳሌም የእናታችን ድንግል ማርያም መቃብር የሚገኝበት ቤት ክርስትያን (ጌቴ ሰማኔ )ከነዛ የማህበሩን ኣገልግሎት ተጠቃሚ ለመሆነ ዕድል ያገኙት ቤተክርስትያን ኣንዷ ናት።

ማህበረ ኣቡነ ሰላም እሳራኤል መምህራችን እና ኣባታችን ኣባ ሳሙኤል ፡ዶክሜንቴሽን ክፍልና ፣እስከ 50 የሚደርሱ የኣገልግሎት ክፍል የሚገኙበት የእረፍት ግዜኣቸዉን መስዋእት በማድረግ የጉልበት ኣገዝ ኣድረጉ። ኣርማንያዊው የቤተ ክርስትያኑ ኣስተዳደር በሰጡት ቃል በዚ ማህበር ያገኙት ድጋፍ በጣም እያመሰገኑ ሰራው በገንዘብ ቢተመን በጣም ብዙ ዉጪ ይጥይቃቸው እንደነበረ ሁኖም ግን ብዚ ኣሁን ግዜ እንደዚ ኣይነት ማህበር(ትርፉ ሰመያዊ ብቻ የሆነ)ማህበር ለማግኘት ከባድ በሆነበት ግዜ ድንግል ማርያም እራሷ በግዜውና የሚገባቸዉን ማህበር እንዳዘጋጀችላቸው መሰከሩ።

ኣባታችን እና መምህራችን ኣባ ሳሙኤል ከስራው ብሆላ በሰጡት ትምህርት ማህበራችን ሁሌም ለበጎ ሰራ ዝግጁ መሆን እንዳለብን ኣስረዱ።

ዘብፁዕ ወቅደስ አቡነ ማትያስ ቀዲማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሉቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ 

ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት

የ2006 ዓ/ም ኣስመልክተው መልእክት ኣስተላለፉ

 

ሪፖርትራችን ከዛቦታ እንደገለጠው ብፁዕ ወቅደስ አቡነ ማትያስ ቀዲማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ መልእክታቸዉን የዘመናት ፈጣሪ እግዚአብሔር አምላካችን፣እንኳን ከሁለት ሺ አምስት ዓመተ ምሕረት ዘመነ ማቴዎስ ወደ ሁለት ሺ ስድሰት ዓመተ ምሕረት ዘመነ ማርቆስ በሰላም አደረሳችሁ!!ብለውከጀመሩ በኋላ። አምላካችን እግዚአብሔር፣ለፍጡራን ከሰጣቸው መልካም ስጦታዎች መካከል፣የዘመን ስጦታ የመጀመሪያ ውን ደረጃ እንደ ሚይዝ እንዳስረዱ ገለጠ።

Publication3

          

         ከዛም በመቀጠል ከ(ዘፍ.2÷15) በመነሳት እግዚአብሔር፣ ዘመናትን በሰዓታት፣ በቀናት፣ በወራት በወቅቶችና በዓመታት፣ ከፋፍሎ የፈጠረበት ዋና ምክንያት፣ በእነርሱ መለኪያነት፣ አቅደን፣ አልመንና ጠንክረን በመሥራት፣ ራሳችንን፣ ቤተ ሰባችንን፣ ሀገራችንንና ሃይማኖታችንን በአጠቃሊይ ዓለማችንን፣ ለኑሮ የተመቸች፣ ውብና ለም አድርገን እንድንከባከብና እንድንጠብቅ ነው ኣሉ ፡፡

           ረፖርተሩ በመቀጠል ብፁዕ ወቅደስ አቡነ ማትያስ ቀዲማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ በመልእክታቸው የዘመን ጸጋ፣  በሥጋዊ ሕይወታችን ብቻ ሳይሆን፣በመንፈሳዊ ሕይወታችንም  ከፍተኛ ትርጉም እንዳለው፤ የእግዚአብሔር ቃል፣ እንደነገረን፣ ዘመናት እግዚአብሔርን ፈልገን ለማግኘት የሚያስችለን መሣሪያዎች እንደሆኑ፤ ይህም ማለት፣ እያንድኣንደ ዓመት፣ በሰው አእምሮ ውስጥ ጥሎት የሚያልፍ፣ ተግባራዊ ትምህርትና ዕውቀት እንዳለ፤ ከዚህ አኳያ፣ ሰው፣ በየዓመቱ ከሚቀስመው ሰፊ ግንዛቤ፣ ዕውቀቱን እያሰፋ፣ ወደ ተሻለ ማስተዋል እንደሚሸጋገር፤ ጤናማ ማስተዋልን ሲያገኝ፣ ፈጣሪውን ወደ መፈለግና ወደ መከተል፣ ፍጹም ሰው ወደ መሆንም እንደሚደርስ፤ በዚህ ምክንያት፣ ዘመን፣ ሰው፣ ፈጣሪውን እንድያውቅ የሚያስችል፣ የማብቃት ጸጋ እንዳለው ተንትነው እንዳስረዱ ገለጠ ።

በመጨረሻም ኣዲስ ዘመን ለመላ የክርስትና እምነት ተከታዮች የሰላምና የብልጽግና ዘመን እንዲሆን ጠንከረን መስራት እንዳለብን መልእክታቸዉን እንደኣስተላለፉ ኣስረዳ።

ብኣባ ሳሙኤል የተደረሱት መጽሓፎችና የታተሙ የስብከት ሲዲዎች ለመእመናን መንፈሳዊ ሂወታቸውጋ ብዙ ኣበርክቶ እያደረጉ ናቸው

 

በተለያዩ ግዜ በኣባታችንና መምህራችን ኣባ ሳሙኤል ወልደ ሰላማ የተደረሱ መጽሓፎችና የታተሙ የስብከት ሲዲዎች ለመእመናን መንፈሳዊ ዕድገት በጣም ብዙ ኣበርክቶ እየተጫወቱ መሆናቸዉን ዶክሜንተሽን ክፍል ማህበር ኣቡነ ሰላማ ባወጡት መግለጫላይ ኣስረዱ።

Publication2

እስካሁን በኣባታችንና መምህራችን ኣባ ሳሙኤል የተደረሱ መጽሓፎች ትምህርት ሃይማኖት፣ገድለ ኣቡነ ሰላማ በትግርኛና በግዕዝ፣መልዕ ኣቡነ ሰላማ በኣማርኛ በትግርኛና በግዕዝ፣ውዳሴ ማርያም በትግርኛ እንዲሁም መልክዕ ሰማእቷ ቅድስት ኣርሴማ በኣማርኛና በትግርኛ ሲሆኑ እስካሁን እስከ 5 የሚሆኑ የስብከት ሲዲዎች ለመእመናን እንደቀረቡ የሚታወቅ ነው።

     ስለዚ ኣስመልክተን ያናጋገርናቸው መእመናን ሲመልሱ ‘’ይሄን ሃብት ለሰጣቸው እግዚኣብሔር እያመሰገኑ እነዛ መጽሃፎች ይሁኑ የስብከት ሲዲዎች መንፈሳዊ ሂወታቸዉን በጣም ብዙ እንደሚያግዟቸው ኣረጋገጡ ፣በመቀጠልም ከሌላ መጽሃፎች ለየት የሚያደርጋቸው እነዚ የኣባ ሳሙኤል መጽሃፎች በቛንቛችን የተጻፉ በመሆናቸው ለመገልገያ ቀለል እንደሚላቸው ገለጡ።

ኣባታችንና መምህራችን ኣባ ሳሙኤል ስለዚ ኣስመልክተው በሰጡት መግለጫ ፣ይሄን ዕድል ለሰጣቸው እግዚኣብሔር እያመሰገኑ ፣ጸሎት በምታውቀው ቋንቋ ከጸሎት በማታውቀው ቋንቋ በበለጠ የእግዚኣብሔርንና ይቅዱሳን ፍቅር እንድያድርብህ እንደሚያግዝ ኣስረዱ፣ከሱ ጋር ኣያይዘእው መእመናን እግዚኣብሔር የሰጣቸዉን እድል ተጠቃሚ ሁነው፣ለነዛ ለዚ እድል ተጠቃሚ ላልሁኑት ቤተሰባችን ተጠቃሚ ማድረግ እንዳለብን መልእክታቸዉን ኣስተላለፉ።

በቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስትያን ኢትዮጵያ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ምስል ያለበት መስቀል ከስማይ እንደወረደ ተገለጠ

 

ገላንጉራፈለገግዮንቅዱስገብርኤልቤተክርስቲያንብርሃንየተሞላመስቀልከሰማይ እነደ ወረደ” የተለያዩ ምንጮች መግለጥ ላይ ይገኛሉ።

ከአዲስ አበባ የመጡ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት በገላን ጉራ ፈለገ ግዮን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ተከሰተ በተባለ ተአምር መስቀሉ ወረደ የተባለው ሐሙስ ለአርብ አጥቢያ ከለሊቱ 9፡00 ሰዓት አከባቢ ነሐሴ 23 ቀን 2013 ሲሆን ካህናት አባቶች እና ምእመናን የክርስቶስ ሳምራን የበአል ዋዜማ ማህሌት ቆመው እንዳለ መስቀሉ መውረዱን ተንትነዋል ።

ስፍራው የተገኘው መረጃ እንደሚጠቁመው ማህሌት ቆመው የነበሩት አባታኦች ከሰማይ የወረደውን መስቀል ድምፅ ሲሰሙ ካህናትና የቤተክርስቲያን አስተዳደሩ ከቤተመቅደስ ወጥተው ሁኔታውን ሲመለከቱት ብርሀን ከሰማይ እንደወረደና አከባቢውን በብርሀን እንደሞላው እንደ ተመለከቱ። መስቀሉ የጌታ ስቅለት ያለበት እንደሆነም መረጃው ያረጋግጣል።

Publication4

ከሱ ጋር ኣያይዞም ይሄ በታኣምር ከሰማይ የወረደኣው የጌታችን መስቀል በብጹእ ወቅዱስ ኣቡነ ኢስቲፋኖስ በዕለት 27 ነሃሰ 2005 ዓ/ም ተነስቶ በክብር ወደ ቤተ መቅደስ እንደገባ ዘግብዋል።

6ኛው ዙር መንፈሳዊ ኮርስ ቅዱስ ቁርባን ማህበር ኣቡነ ሰላማ ተጀመረ

 

ብዙ ይጠበቅ የነበረው 6ኛው ዙር መንፈሳዊ ኮርስ ቅዱስ ቁርባን እንደ ተጀመረ የማህበር ኣቡነ ሰላማ የትምህርት ክፍል ገለጠ።

ቅዱስ ቁርባን ማለት ለእግዚኣብሔር የሚቀርብ ኣምሃ፣መስዋእት፣ መንፈሳዊ ነገር ሁሉ ማለት ሲሆን፣ተማሪዎች ሰለዚ ሚስጥር ሰፋ ያለ እውቀት እንዲኖራቸው ማህበሩ ቡዙ ወጮች በጣም ብዙ የግዜ መስዋእት እንደሚደርግለት የትምህርት ክፍል ሃላፊ የሆኑት መም ተስፋኣለም ገለጡ።

መም ተስፋኣለም መግለጫቸው ላይ እንደገለጡት ይሄ በኣባታችንና መምህራችን ኣባ ሳሙኤል ዘውትር ማክሰኞና ሓሙስ የሚስጠው ያለው የቅዱስ ቁርባን ትምህርት ፣ሁሉም ተማሪዎች ክብርና ጥቅም በሚገባ ኣውቀው ከፍ ያለ ጥንቃቔ ማድረግ እንዳለባቸው ኣስረዱ።

ኣባታችናና መምህራችን ኣባ ሳሙኤል በበኩላቸው ቅዱስ ቁርባን ማለት በወንጌል ተምረህ ፣በንሰሃ ታጥበህ ሰወስተኛውና የመጨረሻው ደረጃ መሆኑን ኣስረዱ ስለዚህም ተማሪውች በጥንቃቄ ትምህርታቸዉን መከታተል እንዳለባቸው መልእክታቸዉን ኣስተላለፉ ።

ኣባታችናና መምህራችን ኣባ ሳሙኤል ኮርሱ ተማሪዎቹ ቅዱስ ቁርባን ከመወሰዳቸው በፊት ያለዉን ዝግጅት፣ በተቀበሉበት ግዜ ማድረግ የሚገባቸዉን ጥንቃቄ ፣ከተቀበሉ በሆላ ያለው ሂወታቸው እንዴት መሆን እንዳለበትና ፣ከቅዱስ ቁርባን የሚገኘዉን ጥቀም ያካተተ መሆኑን በዝርዝር ኣስረዱ።

ዘውትር እሮብ ሃይማኖታችንን እንወቅ በሚል ኣርእስት የሚሰጥ ያለው ትምህርት እየቀጠለ ነው።

ማህበር ኣቡነ ስላማ በመስራችና መሪ ኣባታችን ኣባ ሳሙኤል ወልደ ሰላማ ሃይማኖታችንን እንወቅ በሚል ኣርእስት የሚሰጠው ያለው ኮርስ ለ1 ዓመት እንደቀጠለ የማሕበሩ ኮሚቴ ገለጸ።

 ኮርሱ የሚስጠው ያለው ለኣገልግሎት ክፍል፣ለዘማሪዎችና፣ለኮሚቴ እንደሆነ የገለጠው ኮሜቴ ማህበር እስካሁን 2 ኮርስ እንደጨረሱና ሶወስተኛዉን ኮርስ ላይ ኣንዳሉ ገለጸ ።ኮሚቴው ከሱ ጋር ኣያይዞ ትምህርቱ ዕውቀትና ደረጃ የተማሪዎችን ግምት ላይ ያስገባ በምሆኑ በጣም ብዙ ፍሬ እየታፈሰባት ምሆኑን ኣስረድቱዋል ።እዚ ከ100 ተማሪዎች በላይ የሚግኙበት ኮርስ እስካሁን ሃይማኖት፣ነገረ ማርያምና የመጽሃፍ ቅዱስ ጥናት የምል ኣራስቶች እንደተማሩ መልዕክቱ ይገልጻል ።

         ተማሪዎቹ ይሄንን ዕድል ለሰጣቸው ኣግዚኣብሄር እያመሰገኑ በሚያገኙት ያሉት ትምህርት ቤት ክርስትያናቸዉን ለመርዳት እንደሚያግዛቸኣው ገለጡ።

         መስራችና መሪ የሆኑት ኣባ ሳሙኤል መልዕክታቸው ጋር እንደገለጹት “በዙ የለፋህበት በዙ ፍሬ የገኝበታልና” ፣በጣም በዙ ለውጦች ተማሪዎቻቸው ጋር እንዳዩ ገልጸዋል ፣ከሱ ጋር ኣያይዘው ኣባ ሳሙኤል ተማሪዎቹ ለዚ ለቅዱስ ቁርባንና ለሚያሳዩት ትልቅ የባህሪ ለውጥ ምክንያት ከእግዚኣብሔር ሃይል ብኋላ ፣በቃል ማስተማር ብቻ ሳይሆን ኣካሄዳቸዉን በማጥናት ክትትል በምድረግም እንደሆነ ገልጸዋል ።ከሱ ጋር ኣያይዘኣው ኣባ ሳሟኤል መማህራን የተማሪዎቻቸው ኣብነት በመሆናቸኣው መምህሮች ኣያደረጉ ኣድርጉ ማለት እንዳለባቸው ኣያይዘኣው ኣስረድተዋል።

                     ወስብሓት ልእግዚእብሄር!!!!

 

በግብጻውያን የክርስትና እምነት ተከታዮች ከፍተኛ ጥቃት ተፈጸመባቸው

በኮፕት ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስታይን የሚታወቅ ከኣምስቶች እህታማሞች ቤተ ክርስያን ኣንዷ የሆነችው የግብጽ ቤተ ክርስትያን ባለፈው ሳምንቶች በፕሬዝደንት መሓመድ ሞርሲ ደጋፊዎች የሆኑት የሞስሌም ወንድማማቾች የፖለቲካ ሽፋን በማድረግ የሽሪዓ መንግስት ለመትከል ያላቸዉን ህልም ለመፈጸም ከፍተኛ ጥቃት እንደ ደረሰባት የተለያዩ የዓለም ኣቀፍ የመረጃ ምንጮች በመግለጽላይ ናቸው።

       download

 

         እስካሑን እሰከ 17 ቤተ ክርስትያን ጥቃት እንደደርሰባቸው የሚታወቅ ሁኖ ፣የሚና ቅድስት ማርያም፣ የኣብርሃም ቤተ ክርስታይንና የማር ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስትይን ከነዛ ጥቃት የደረሰባቸው ጥቂቶች ናቸው።ከካይሮ የሚወጡ ኣዳዲስ መረጃዎች ኣንደሚያረጋግጡት በላይኛው ግብጽም በርክታ ኣብያተ ክርስትያናት የተቃጠሉና ጥቃት እየደረሰባቸው ሲሆን ብዙዎች ክርስትያኖችም እየተገደሉ መሆኑን መረጃዎች ይጠቁማሉ፣በዚህም ምክንያት ብዙዎች ክርስትያንኖች መኖርያቸውንና የስራቦታቸዉን እየለቀቁ መሰደዳቸዉን ይነገራል።ኣብያተ ክርስትያናትም ኣገልግሎታቸዉን ማቋረጣቸዉን ዓለም ኣቀፍ የዜና ምንጭች እየዘገቡ ይገኛሉ።  

 

           ይሄ ሁሉ በሚሆንበት ያለው ግዜ ግብጻውያን ከርስትያኖች በኣባቶቻቸው ኣማካይነት (የሰራነዉን ቤት- ክርስትያን ያቃጥሉ የሰራነዉን ሰመያዊ ቤት ግን በፍጹም ኣይደርሱበትም ፣ንብረታችንን ይወስዳሉ እምነታችንን ግን ኣያገኟትም ፣እኛን ይገድላሉ ነፍሳችንን ግን ፣ከኣቅማቸው በላይ ናት፣ መስቀል ለመሽከም ዝጉጁ ነን)የሚል መልእክት ወደ ዓለም ህዝብ ኣያስተላለፉ ይገኛሉ ።

                    popetawadros  

 

             በዚህ ኣጋጣም የማህበረ ኣቡነ ሰልማ መስራችና መሪ የሆኑ ኣባ ሳሙኤል ወልደ ሰላማ ለሙሉ የማህበሩ ኣባል በጸሎት የግብጽን ቤተ ክርስትያን እንድያስታውሱቸው፣ኣንዲሁም የጥናት ይስጣቹህ መልእክታቸዉን ለመላ ይግብጽ የክርስትና እምነት ተከታዮች ኣስተላልፈዋል።

 

                             ወስብሃት ለእግዚኣብሄር

 

 

 

 

ጌታችንና መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መለኮትነቱን የገለጠበት ታላቁ ባኣል ደብረ ታቦር በድመቀ ሁኔታ ተከበረ

መሃበረ ኣቡነ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ክብረመንግስቱን ብርሃን መልኮቱን የገለጠበት ፣በየዓመቱ 13 ነሓሴ ቀን ቤተ ክርስትያናችን ከምታክብራቸው ዘጠኙ ብኣላት ኣንዱ የሆነው ደብረ ታቦር በደመቀ ሁኔታ እንዳከበረ ተገለጠ።

   images

 

  ከዶክሜንቴሽን ክፍል የተገኘው መረጃ ኣንደሚያመለክተው ማህበር ኣቡነ ሰላማ ከ300-400 የሚሆኑ መእመናን እስክትሎ ተጉዞ ክብረብዓሉን ኣማናዊ ደብረ ታቦር ተራራ ላይ እዳከበረው ያስረዳል ።ጠዋት 7,00 ስዓት በኣባታችንና መምህራችን ኣባ ሳሙኤል ጸሎትና ኣጭር መግለጫዎች ስለመንገዱና ስለባኣሉ ኣስመልክቶ ከተሰጠ ቡሃላ ልክ 9,0 ስዓት ላይ ማህበር ኣቡነ ሰላማ ጉዞዉን ወደ ደብረ ታቦር ኣንዳደረገ ማስረጃው ጨምሮ ያስረዳል።ከ2-3 ሰዓት መንገድ ጉዞ ቡሃላ ማህበር ኣቡነ ሰላማ ዳቦር ከተማ እንደደረሰ ጨምሮ ዘግብዋል።

     ከዛ ቦታ ካሉ ምንጮች ኣንዲሚያረጋግጡት ማሕበር ኣቡነ ሰላማ በኣባታችንና መምህራችን ኣባ ሳሙኤል መሪነት ተራራዉን በእግራቸው ኣየዘመሩ ተሰቀሉ፣ተራራው ዳገታምና ኣድካሚም እንዃ ቢሆን የዓመት በረከት ነው በማለት ማህበር ኣቡነ ሰላማ በደስታ እንደተጓዘ ምንጮች ጨምረው ዘግብዋል ።ቤተ ክርስትያን ከተሳለመ ቡሃላ ማሃበር ኣቡነ ሰላማ ጉባኤዉን በድብረ ታቦር ተራራ ላይ ብኣባታችንና መምህራችን ኣባ ሳሙኤል በጸሎት ከፍተው ጀመሩት በተከታታይ ስለ ብኣሉ የሚመለከት መዝሙሮች ከቀረቡ በኋላ ፣ቃለ ኣግዚኣብሄር ብኣባታችንና መምህራችን ኣባ ሳሙኤል ኣስፍተውና ኣመሳጥረው ለመእመናን ከቀረቡት መደቦች ጥቂቶች ናቸው። በጸሎት የጀመረው ጉባኤ በጸሎት በኣባታችንና መምህራችን ኣባ ሳሙኤል ኣንደዘጉት ኣያይዘው ገልጥዋል።

   ማህበር ኣቡነ ሰልማ ልክ 3፣00 ሰዓት የከሰዓት ጉዞዉን ወደመጣበት ኣደረገ እንደኣመጣጡ ሲመለስም ኣባታችንና መምህራችንን ኣባ ሳሙኤል እይተከተለ ማህበሩ እየዘመረ ከተራራው ወርዶ ወደ ያቶቢሱ ተሰቅሎ መንገዱን ወደ ቴል ኣቪቭ እንደጀመረ ምንጮቻችን ኣስረድትዋል።ማህበር ኣቡነ ሰላማ ከደብረታቦር ወደ ቴል ኣቪቭ በሚመልስበት ግዜ መንገድ ላይ እርፍት በማድረግ የተዘጋጀለትን የዛን ቀን እለት ኣንግዶት ተስተናግዶ ወደመጣበት ቦታ በሰላም እንደተመለሰ መረጃዎች ያስረዳሉ።             ወስብሃት ለእግዚኣብሄር !!!    

መደቦቻችን

No events

የመፅሓፍ ቅዱስ ጥቅስ

readings "  በጌታ የተወደዳችሁ ወንድሞች ሆይ፥ ሁልጊዜ ስለ እናንተ እግዚአብሔርን ልናመሰግን ግድ አለብን፥ እግዚአብሔር በመንፈስ መቀደስ እውነትንም በማመን ለመዳን እንደ በኵራት መርጦአችኋልና"   

              2ኛ ወደ ተሰሎን 2:13

በኣባ ሳሙኤል የቀረቡ መፃህፍትና ቪቺዲዎች

abb 1

ካባቶኣንደበት

stanthony"ለእግዚኣብሄር ከወንድምህ በላይ ውደደው ለወንድምህ ደሞ ከነፍስህ በላይ ውደደው"   ኣባ ይስሓቕ ሶርያዊ

ካባቶች ምክር

stanthony"ኣንዲት የክፋት ቃል ለመልካም ሰው ክፉ ታደርገዋለች፥ ኣንዲት መልካም ቃል ግን ለ ክፉ ሰው መልካም ታደርገዋለች።"    ኣባ መቃርዮስ 

saying fathers

stanthony"If then we have angels, let us be sober, as though we were in the presence of tutors; for there is a demon present also."   John Chryssostom

saying of fathers

stanthony"Let books be your dining table, / And you shall be full of delights. / Let them be your mattress,/And you shall sleep restful nights"   Ephraim the Syrian

 

              በነዚ ላይ በመጫን ይከተሉን

  twitter-logo-circular-OFFfacebThis email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.

adress