christmas star Mahbere Abune Selama- self help association, support those in need, Spiritual gatherings, youth and adult counselling  christmas star

lo 1

የማሕበሩ ስራዎች              

1.የማሕበሩ ቦርድና ስራ አመራር ኮሚቴ


y¥?b„ x-”§Y XNQS”s@ bmöÈ-R ›m¬êE XQD bjT b¥}dQ እንዲሁም y¥?b„ Ä!s!pEl!N bmöÈ-R Ys‰LÝÝ XNÄ!h#M y¸zU° y?TmT ý-@èC bmgMgM ¥St¥¶Ã XNÄ!çn# ÃdRULÝÝ kz!H bt=¥¶ byï¬W N;#úN ¥:k§T b¥êqR ¥?b„ XNÄ!sÍ ያደርጋልÝÝ

2. በማህበሩ ግንኙነት ክፍል የተደረጉ እንቅስቃሴዎች


የግንኙነት ክፍል የማህበሩ አባላት መንፈሳዊ ሂወትን በመከታተል መንፈሳዊ ምክርና ትምህርት የሚያገኙበትን ሁኔታ በማመቻቸት ወደ ንስሃና ቅዱስ ቁርባን እንዲደርሱ አድርጓል።  እያንዳንዱ የማሕበሩ አባል የመልካም አርአያ ተምሳሌት ይሆኑ ዘንድ ክትትልና መንፈሳዊ ድጋፍ አድርጓል፡፡  በተጨማሪም ከቅርንጫፍ ማሕበራት ጋር የጠበቀ ግንኙነት በማድረግ የአሰራር ተሞኩሮና የተለያዩ መንፈሳዊና አስተዳደራዊ መረጃዎችን የተመለከተ የልምድ ልውውጥ አካሂዷል።

3. የቅርንጫፍ ማህበራት እንቅስቃሴ


ማህበሩ በሚያካሂዳቸው መንፈሳዊ አገልግሎቶች አማካይነት የተመሰረቱ ቅርንጫፍ ማህበራት ብዛት በየጊዜው እየጨመረ መጥቷል። በአሁኑ ሰዓት ማህበሩ btlÆ ï¬ãC ቅርንጫፍ ማህበራት ሲኖሩት ወርሃዊ የጸበል ጸዲቅና የስብከተ ወንጌል መርሃ ግብሮችና ሌሎች መንፈሳዊ ትሩፋቶች ይፈጸማሉ። ለምሳሌ ታማሚዎችን መጎብኘትና አጫጭር የጉዞ መርሃ ግብሮች ማከናወን በቅርንጫፍ ማህበራት እየተፈጸሙ ያሉ ተጠቃሽ ክንውኖች ናቸው።

4. በማህበሩ ፋይናንስና ንብረት ክፍል የተደረገ እንስቃሴ

የፋይናንስና ንብረት ክፍል ማህበሩ ከተመሰረተ ጀምሮ ህጋዊ የወጪና ገቢ አሰራር በመከተል የቀን ተቀን ስራውን ያከናውናል። ስለሆነም የተሰጠውን መንፈሳዊ አደራ ይበልጥ ለመጠበቅና አርአያ ሆኖ ለመገኘትም በህጋዊ የውጭ የሂሳብ አዋቂዎች በኩል አጠቃላይ የማህበሩ የሂሳብ ስራ በየዓመቱ እንዲመረመር ያደርጋል። ውጤቱንም በዚህ መሰረት ለመላው አባላቱ በግልጽ በማቅረብ አጽድቋል፡፡ በአሁኑ ወቅት የማህበሩ የበጀት ዓይነቶች ሰባት ሲሆኑ የፋይናንስ ክፍሉ ከአባላቱ በሚያገኘው መዋጮ ህጋዊ የገቢና የወጪ ደረሰኝ ተጠቅሞ ስራውን ያከናውናል።

5. የልማትና ተራድኦ ክፍል

ከአባላት በሚገኝ ገንዘብ፣ ንብረት፣ ጉልበትና እውቀት ለተለያዩ ገዳማትና አድባራት እገዛ እያደረገ መጥቷል። በዚህ መሰረት ባለፉት ዓመታት እገዛውን ካገኙ አብያተ ክርስቲያናትና ገዳማት ብዙ ናቸው።

6. በግብረ ሰናይ ንዑስ ክፍል ለችግረኞች የተደረገ ድጋፍ

በግብረ ሰናይ ንዑስ ክፍል በሦስት መንገዶች በሽተኞችንና የተቸገሩ ወገኖችን ይረዳል።  እነሱም በሆስፒታል፣ ጠበል በሚጠመቁባቸው አብያተ ክርስቲያናት ለሚገኙ ታማሚዎችና በየመኖሪያ ቤታቸው ሆነው በሕመም ለሚሰቃዩ ወገኖች በመጠየቅ የሚደረግ ድጋፍ ነው። 

በዚህ መሰረት ማህበሩ ከተቋቋመ ጊዜ ጀምሮ ኣባላቱ በእረፍቱ ቀን ከጉባኤ በኋላ በሆስፒታል በመገኘት ታማሚዎችን ይጎበኛሉ። በተጨማሪም በሆስፒታል በየቤታቸውና በጸበል ቦታ ለሚገኙ በሽተኞች መንፈሳዊ ምክር በመስጠት፣ ወደ ጸበል ቦታ ማመላለስ፣ ሃዘንተኞችን በማጽናናት፣ አቅም ለሌላቸው የቤት ኪራይ በመክፈል፣ በወር ኣንድ ጊዜ የተቸገሩ ወገኖች ምግብ በማዘጋጀት ወንጌል በማስተማር እገዛ ያደርጋል።

7. በጸበል ክፍል የተደረገ እንቅስቃሴ

በአቡነ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን ስም ዝክር በማድረግ የቅድስት ኪዳነ ምህረት፣ የቅድስት አርሴማ፣ የቅዱስ ሚካኤልና የአቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ፣ የቅድስት ሃናና የቅዱስ ኢያቄም ገድላቸውና ተአምራታቸው እንዲነበብ በማድረግና ቃለ ወንጌል በማስተማር የማሕበሩ አባላት ከቅዱሳኑ በረከት እንዲሳተፉ አድርጓል፡፡   

በአጠቃላይ በተለያዩ ዓመታዊ በዓላት ማለትም በፋሲካ፣ የአቡነ ሰላማ ሐምሌ 26 ዓመታዊ በዓል፣ ዘመን መለወጫ፣ በጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓልና በተለያዩ ክብረ በዓላት ለነዳያን የምሳ መስተንግዶ በማዘጋጀት፤እንዲሁም የልብስ፣ የስዕለ አድህኖና የጸሎት መጽሐፍት በማበርከት እገዛ በማድረግ ላይ ይገኛል።

8. ዲኮሬሽን ክፍል

ይህ ክፍል በተለያዩ ወርሃዊና ዓመታዊ በዓላት የጉባኤ መድረኩን በማጽዳትና በማስዋብ ለመንፈሳዊ ትምህርት ስኬት አይነተኛ አስተዋጽኦ የሚያደርግ ክፍል ነው። በተለይም ምእመናን የመድረኩን የተለያዩ ዝግጅቶች በተመስጦ ለመከታተል ያስችላቸው ዘንድ አስፈላጊ ጥቅሶች፣ ቅዱሳን ስእላትና እንደ ግብአት ሆነው የሚያገለግሉ የድምጽና የመብራት ቅንብሮች በማዋሃድ በርካታ ስራዎች የሚያከናውን ክፍል ነው።

9. የመረጃ ዶኩመንቴሽን ክፍል እንቅስቃሴ

     የመረጃ ክፍሉ የስራ እንቅስቃሴ የማሕበሩን አጠቃላይ ስራዎች በምስል /በቪድዮና ፎቶ ግራፍ/፣  በድምጽ /ሲዲዎችና ካሴቶች/ በጽሑፍ /በብሮሸርና መጽሔት/ የተለያዩ አስፈላጊ መረጃዎችን ማሰባሰብ የሚጠቃልል ነው።  ገድልና መልክዕ፤ ውዳሴ ማርያም ኣዘጋጅቶ ኣቅርቧል። 

10. ኪነ  ጥበብ  ክፍል

ኪነ ጥበብ ማለት የልዩ ልዩ ተግባረ እድ የዜማ፣ የግጥም፣ የድርሰት፣ የዝማሬ ሙያና ስራ ነው፡፡ ኪነ ጥበብ ክፍል በማህበሩ ካሉት የአገልግሎት ክፍሎች አንዱ ሲሆን በፕሮግራምም ላይ መድረክ ከመምራት እሰከ ትምህርት የሚሰጥበት ጊዜ ድረስ ያሉትን የመድረክ ስራዎች ያከናውናል፡፡


ይህ ክፍል በውስጡ መዘምራን፣ ድራማ ክፍል፣ ስነ ፅሑፍ ክፍል  የያዘ ነው፡፡ እንደ አስፈላጊነቱም በቅርንጫፍ ማህበራት በመገኘት  የመዝሙር፣ ድራማ ስነ-ጽሁፍ፣ የትረካ አገልግሎት እየሰጠ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪም የተለያዩ ኮርሶችን ሰጥቷል፡፡ ለምሳሌ የመንፈሳዊ መሳሪያ ስልጠና ዋሽንት ማሲንቆና ክራር፣ እንዲሁም ልዩ መርሐ ግብር በማዘጋጀት ክፍሉን ለማሳደግ ጥረት እያደረገ ይገኛል፡፡

11. የማሕበሩ የወደፊት ትኩረት

ማሕበሩ የጀመራቸውን የበጎ አድራጎት ስራዎች በበለጠ አጠናክሮ ይቀጥላል፡፡

መደቦቻችን

No events

የመፅሓፍ ቅዱስ ጥቅስ

readings "  በጌታ የተወደዳችሁ ወንድሞች ሆይ፥ ሁልጊዜ ስለ እናንተ እግዚአብሔርን ልናመሰግን ግድ አለብን፥ እግዚአብሔር በመንፈስ መቀደስ እውነትንም በማመን ለመዳን እንደ በኵራት መርጦአችኋልና"   

              2ኛ ወደ ተሰሎን 2:13

በኣባ ሳሙኤል የቀረቡ መፃህፍትና ቪቺዲዎች

abb 1

ካባቶኣንደበት

stanthony"ለእግዚኣብሄር ከወንድምህ በላይ ውደደው ለወንድምህ ደሞ ከነፍስህ በላይ ውደደው"   ኣባ ይስሓቕ ሶርያዊ

ካባቶች ምክር

stanthony"ኣንዲት የክፋት ቃል ለመልካም ሰው ክፉ ታደርገዋለች፥ ኣንዲት መልካም ቃል ግን ለ ክፉ ሰው መልካም ታደርገዋለች።"    ኣባ መቃርዮስ 

saying fathers

stanthony"If then we have angels, let us be sober, as though we were in the presence of tutors; for there is a demon present also."   John Chryssostom

saying of fathers

stanthony"Let books be your dining table, / And you shall be full of delights. / Let them be your mattress,/And you shall sleep restful nights"   Ephraim the Syrian

 

              በነዚ ላይ በመጫን ይከተሉን

  twitter-logo-circular-OFFfacebThis email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.

adress