christmas star Mahbere Abune Selama- self help association, support those in need, Spiritual gatherings, youth and adult counselling  christmas star

lo 1

cross animation smallውግዘት ያስፈልጋልን? cross animation small

 

አዎ! ውግዘት አስፈላጊነቱን በሚገባ ጠንቅቀን እንረዳዋለን ግን ለማን? አንድ ምእመን ከሃይማኖት ወጥቶ፤ ከምግባር አድጦ ሲገኝና ተመክሮ አልሰማም ሲል ከሕዝበ ክርስቲያን እንዲለይ በሥልጣነ ክህነት የሚፈጸም መንፈሳዊ ቅጣት ነው፡፡ ማውገዝ ወደ ገሃነም የሚያወርድ ፍርድ በመሆኑ በችኮላ መደረግ የለበትም፡፡ ያለ በቂ ምክንያት፤ ያለ በቂ መረጃና ትዕግስት በሰው ላይ ይህንን ያህል ጭካኔ ማድረግ አይገባምና፡፡  ከማውገዝ አስቀድሞ በትዕግሥት መላልሶ ማስተማር፤ ሳይታክቱ መምከር፤ እምቢ ያለ እንደሆነ መገሰጽ ያስፈልጋል፡፡ ከዚህ በኋላ እንደ ጥፋቱ አይነት እያዩ መታገስ በቂ ጊዜ መስጠት ተገቢ ነው፡፡ ፈጣሪ ለሰው አዛኝ፣ ሩህሩህና መሐሪ ስለሆነ ከሰዎች መካከል አንድም እንኳን እንዲጠፋበት አይፈልግም መጽሐፍ ቅዱስ ሰው ሁሉ ለቁጣ የዘገየ ይሁን ብሎ ይመክረናል፡፡

                  6  Bible paintings Kebran Gabriel JPG               

                                 

 

                                    ውግዘት ለማን?

 

እምነት አለኝ የሚል ሥራ ግን የሌለው ሰው

ለምሳሌ፡- አውዶክሲያ የተባለች ንግሥት የድሃ መሬት በግፍ በቀማች ጊዜ የድሆች ጠበቃ የተሰኘው ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ (Golden Mouth) አውግዟታል፡፡ ነገር ግን ይህን ያደረገው ድንገት ደርሶ ሳይሆን ከተበዳሪዋ ድሃ ጋር ለማግባባትና ለመገላገል አስፈላጊውን ጥረት ሁሉ ካደረገ በኋላ ነበር፡፡ 

የኢየሱስ ክርስቶስን አምላክነት ለማይቀበል ሰው

መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚነግረን በወልድ ያላመነበአንዱ በእግዚአብሔር ልጅ ስላላመነ አሁን ተፈርዶበታል’’ (ዮሐ 318) ይህ ፍርድ ዕለተ ኩነኔን ውይም ዕለተ ምጽአትን  አይጠብቅም፡፡ ቃሉ የሚለው ወድአ ተኮነነ ማለትም አሁን ተፈርዶበታል  ነውና፡፡ በወልድ ያመነ ግን ሥራው ተመርምሮ ፍርድ ለማግኘት ዕለተ ሞቱን ወይም ምጽአትን ይጠብቃል፡፡ ይህ ፈጣሪ ለሰው ልጆች የወሰነውን የፍርድ ሂደትንም ያሳያል፡፡ የሚያወግዝ ሰው የምግባር ችግር ያለበትን ሰው በትዕግስት ሊጠባበቁት የሃይማኖት ችግር ያለበትን ሰው ግን በቶሎ እርምጃ ሊወስዱበት እንደሚገባ ኣያሳይምን? ቀደም ሲል እንደ ተብራራው ውግዘት ፍርድ ነውና፡፡

ቅዱሳን አባቶች ጥፋተኛን ሰው አውግዘው ከመለየታቸው በፊት ፍጹም ትዕግሥት ያሳዩ ነበር፡፡ ትዕግሥታቸው አግባብ የሌለው እስኪመስል ድረስ ይታገሱ ነበር፡፡ ለምሳሌ ሰለስቱ ምእት አንዲት ነፍስ እንዳትጠፋ ከነበራቸው የእምነት ግዴታ አንጻር በአርዮስ ምክንያት በኒቂያ በተሰበሰቡ ጊዜ ምልአተ ጉባኤ ሲሆን አርዮስን ከማነጋገርና ከማውገዛቸው በፊት ከመስከረም 21 እስከ ሕዳር 9 ሱባኤ ገብተዋል፡፡ አንድ ጊዜ ብቻ ሳይሆን ሁለትና ከዚያ በላይ ተሰብስበው አርዮስን መክረውታል፡፡ ቅዱሳን አባቶች ይህንን ሁሉ ያደረጉት የአርዮስ አንዲት ነስፍ እንዳትጠፋ ተብሎ ነው፡፡

 

Saint John Chrysostom

 

     የቅድስት ድንግል ማርያምን ወላዲተ አምላክነት ለማይቀበል

ንስጥሮስ ተሰምቶ  የማይታወቅ ትምህርት በቤተክርስቲያን አስተማረ ማለትም እመቤታችን ወላዲተ አምላክ አትባልም ብሎ ገልጦ ተናገረ፡፡ በዚህ ክህደቱ በስጋው ብቻ ሳይሆን በነፍሱም እንዳይጎዳ ለዚህ አንድ ፍጡር 200 ጳጳሳት ሰኔ 22/431 . በኤፌሶን ጉባኤ ተደረገ ጉባኤው እንዲደረግ ምክንያት የሆነው የንስጥሮስ ክህደት ነበር፡፡ ተመክሮ ባይሰማ የሃይማኖት ጉዳይ ነውና ከቤተክርስቲያን ተለይቶ ተወገዘ የሚገባ ነውና፡፡ እዚህ ላይ ልብ ማለት የሚያስፈልገው ተጣድፎ ከማውገዝ አጥፊዎች ግለሰቦች የሚመለሱበትን መንገድ ሳይታክቱ ማፈላለግ ቅድሚያ የሚሰጠው መንፈሳዊ ሥራ ነው፡፡ ሳኦል በተደጋጋሚ ፈጣሪን ቢበድልም ቀብቶ ያነገሰው ነቢዩ ሳሙኤል ከፍተኛ ትዕግሥት አሳይቷል፡፡ ከዚህም በላይ ቀን ከሌሊት ከዕምባ ጋር ምህረት እንዲያገኝ ወደ ፈጣሪ ይለምንለት ነበር፡፡

ይህንንም እግዚአብሔር ራሱ በእስራኤል ላይ እንዳይነግሥ ለናቅሁት ለሳኦል የምታለቅስለት እስከ መቼ ነው? እስኪለው ድረስ መደበኛ ስራው አድርጎት ነበር፡፡ ይህን ታሪክ በሚገባ ላሰተዋለው እንኳን ለመንጋ እረኞች ይቅርና ለምእመናንም እጅግ ብዙ ነገር ያስተምራል፡፡ 1 ሳሙ 161 ላይ እንደተጠቀሰው ሁሉ የሃይማኖት ህጸጽ ለተገኘበት ተመክሮ አልሰማም አልመለስም ካለ አውግዘው መለየት እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡ ነገር ግን ያለ አግባብ የሚደረግ ውግዘት አይደርስም ከንቱ ውግዘት ነው ተብሎ ብቻ የሚያበቃ ነገር አይደለም፡፡ በተገዛቹ አይድረስ እንጂ ገዛቹን ሳይጎዳው አይቀርም፤ ያለ አግባብ የሚያወግዝ እራሱ ውግዝ መሆኑ ከመገዘቱ በፊት በጉዳዩ እንዲያስብበትና እንዲታገዝ ያደርገዋል፡፡

ያለ አግባብ ማውገዝ ራስን ማውገዝ እንደሆ ፍትሐነገትስ መንፈሳዊ እንዲህ ይላል፡፡ ኢይስዓር ወኢያወግዝ ዘእንበለ ርትዕ ውእቱኒ ይከውን እሱረ ወውጉዘ፡፡ ይህ በማይገባ አይሰር፣ አያውግዝ፣ በማይገባ ቢያስርና ቢያወግዝ እርሱ ራሱ የታሰረና የተወገዘ ይሆናል ማለት ነው፡፡ /ፍት. ነገ. አን 5/ ምክንያቱም ጸሎት ወደ ራስ ሊመለስ እንደሚችል አታውቅምን? አትጠራጠር ይህ ሊሆን እንደሚችል ቅዱስ ዳዊት ጸሎቴ ወደ ብብቴ ተመለሰ ብሏል፡፡ /መዝ. 3413/ እንዲሁም ሰዎች ባልበደለና ጥፋት በሌለበት ሰው ላይ ውግዘትና እርግማን እንደበረድ ቢያዘንቡበት እንዲጠፋና እንዲጎዳ ቢጸልዩበት ይህ ጸሎትና ውግዘት ተመልሶ አውጋዦቹንና ረጋሚዎቹን ይጎዳል እንጂ ተወጋዡን አይነካም፡፡ ነብዩ ጸሎትየኒ ገብአ ውስተ ሕጽንየ ወይም ጸሎቴ ወደ ብብቴ ተመለሰ ያለው ስለዚህ ነው፡፡ /መዝ 3413/ ድንጋይን ወደ ላይ ቢወረውሩት ወደራስ እነደሚመለስ እንዲሁ ውግዘትና እርግማንን የመሰለ ክቡድ ቃል /ከባድ ቃል/ እግዚአብሔር በማይቀበለው መልኩ ወደ ላይ ቢልኩት ተመልሶ የሚጎዳው ራስን ነው፡፡

ማንም ራሱን ሳያጸዳ የሌሎችን በውሸት በመናገሩ ብቻ ንጹሕ አይሆንም፡፡ ተግሳጻችን ገንቢና ተቀባይነት ያለው እንዲሆን ከፈለግን በመጀመሪያ እኛ ራሳችን  ንጹሕ እውነተኛና በጎ አሳቢ መሆን ይጠበቅብናል፡፡ መልካም እየሰራህ በሐሰት ስትወገዝ ደስ ይበልህ ዝለልም፡፡ ይህ ባንተ የተጀመረ አይደለም ከቀድሞ ጀምሮ ያልተሰደበና ክፉ ስም ያልወጣለት ጻድቅ አይገኝም፡፡ በሐሰት ስትወገዝ ክፉ ስም እንደወጣልህ ያህል ዋጋ ታገኝበታለህና /ሉቃ 622/፡፡

መደቦቻችን

No events

የመፅሓፍ ቅዱስ ጥቅስ

readings "  በጌታ የተወደዳችሁ ወንድሞች ሆይ፥ ሁልጊዜ ስለ እናንተ እግዚአብሔርን ልናመሰግን ግድ አለብን፥ እግዚአብሔር በመንፈስ መቀደስ እውነትንም በማመን ለመዳን እንደ በኵራት መርጦአችኋልና"   

              2ኛ ወደ ተሰሎን 2:13

በኣባ ሳሙኤል የቀረቡ መፃህፍትና ቪቺዲዎች

abb 1

ካባቶኣንደበት

stanthony"ለእግዚኣብሄር ከወንድምህ በላይ ውደደው ለወንድምህ ደሞ ከነፍስህ በላይ ውደደው"   ኣባ ይስሓቕ ሶርያዊ

ካባቶች ምክር

stanthony"ኣንዲት የክፋት ቃል ለመልካም ሰው ክፉ ታደርገዋለች፥ ኣንዲት መልካም ቃል ግን ለ ክፉ ሰው መልካም ታደርገዋለች።"    ኣባ መቃርዮስ 

saying fathers

stanthony"If then we have angels, let us be sober, as though we were in the presence of tutors; for there is a demon present also."   John Chryssostom

saying of fathers

stanthony"Let books be your dining table, / And you shall be full of delights. / Let them be your mattress,/And you shall sleep restful nights"   Ephraim the Syrian

 

              በነዚ ላይ በመጫን ይከተሉን

  twitter-logo-circular-OFFfacebThis email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.

adress