christmas star Mahbere Abune Selama- self help association, support those in need, Spiritual gatherings, youth and adult counselling  christmas star

lo 1

                                          bibአቡነ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን /ፍሬምናጦስ/bib

 

የጻድቁ በረከት ከሁላችን ጋር ይሁንና ታላቁ፣ ስመጥሩ አባታችን ጻድቁ አቡነ ሰላማ 3ኛው መቶ ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ላይ ከአባቱ ከቅዱስ ምናጦስና ከቅድስት እናቱ ማርያም ሰናይት በጢሮስ /ግሪክ/ ተወለደ፡፡  እድሜው ለትምህርት እንደደረሰ በአካባቢው በነበረው ትምህርት ቤት ውስጥ ሃይማኖታዊ ትምህርቱን በሚገባ ተከታትሎ የተማረ በመልካም ሥነ-ምግባርና አስተዳደግ ተኮትኩቶ ያደገ ደግ አባት ነበር፡፡

 

ሜሮጵዮስ የተባለ ነጋዴ /ፈላስፋ/ ወደ ህንድ አገር ሊያልፍ ወዶ ከጢሮስ አገር በጀልባ ጉዞ ጀመረ፡፡  ከእርሱም ጋር ከዘመዶቹ ወገን የሆኑ ሁለት ብላቴኖች ነበሩ፡፡  የአንደኛው ስሙ ፍሬምናጦስ፣ የሁለተኛው ደግሞ ኤዴስዮስ /ሲድራኮስ/ ይባላል፡፡  ሜሮጵዮስ እነዚህን ሁለት ወጣቶች አስከትሎ ወደ አፍሪካ ባህር ጠረፍ በመምጣት በቀይ ባህር ወደብ ውሃ ለመጠጣት እግረ መንገዱንም አገር ለማየት ጀልባውን ጠረፍ ላይ አቆመ፡፡ 

በዚህ ጊዜ በአካባቢው ይኖሩ የነበሩ ሰዎች /የአዱሊስ ነዋሪዎች/ በጀልባዋ ላይ አደጋ በመጣል ሜሮጵያስንና የጀልባዋን ቀዛሪዎች እዚያው ገድለው ሀብታቸውን ዘረፏቸው፡፡  ሁለቱ ወጣቶች ግን ተረፉ፡፡  በማያውቁትም አገር ያለ ዘመድ፣ ያለ ሃብት ብቻቸውን በመቅረታቸው እያዘኑና እያለቀሱ ከዛፍ ሥር ተቀምጠው ሲጸልዩ የአካባቢው ነዋሪዎች ያዟቸውና በጊዜው በአክሱም ነግሶ ለነበረው ለንጉሥ ታዜር በፈረስ አንገት በጦር አንደበት የተማረኩ ሰዎች አመጣንልህ በማለት አስረከቡት፡፡  ንጉሥ ታዜርም በቤተመንግስቱ ውስጥ እንዲያድጉ ፈቀደላቸው፡፡ 

 

AbuneSelamaHawaryeHabesha ከጊዜ ወደ ጊዜ በቤተመንግስቱ ውስጥ ተወዳጅነትንና ታማኝነትን አገኙ፡፡  የአብርሃ እና አጽብሃ አባት የነበረው ንጉሥ ታዜር ኤዴስዮስን ጋሻ ጃግሬ፣ ፍሬምናጦስን በጅሮንድ አድርጎ ሾማቸው፡፡  ንጉሱ ሊሞት በተቃረበበት ጊዜ ልጆቹ ገና አካለ መጠን አልደረሱም ነበርና መንግስቱን በሞግዚትነት እንድትይዝ ለእቴጌይቱ አደራ ሲል ሁለቱን ሶርያውያን ምርኮኞች ግን ነጻ /ሑር/ ለቀቃቸው፡፡  ነገር ግን በእቴጌይቱ ልመና ወደ አገራቸው መመለሳቸው ቀርቶ ልጆቿ እስኪያድጉ ድረስ በአስተዳደር በኩል ሲረዷትና ሲመክሯት ቆዩ፡፡

 

ፍሬምናጦስ በአክሱም በነበረበት ጊዜ የቤተመንግስቱ አማካሪ ብቻ ሳይሆን ቀደም ሲል የኦሪት እምነት በአንድ እግዚአብሄር ማመን እንደነበረ የሚታወቅ ሆኖ የተዋህዶ እምነት ጥምቀትና ክህነትን በሚገባ  የሚመሰረትበትና የሚሰፋበት መንገድ ይፈልግ ነበር፡፡  ያን ጊዜ የነበሩት የኢትዮጵያ ክርስቲያኖች ሐይማኖት ብቻ እንጂ ክህነት፣ ቁርባንና የመሳሰሉት የክርስትና ስርዓቶች አልነበራቸውም፡፡  ልዑላኑ /አብርሃና አጽብሐ/ አካለ መጠን ደርሰው የአባታቸውን መንግስት ሲረከቡ ኤዴስዮስ ወደ አገሩ ተመልሶ ካህን ሆነ፡፡  ፍሬምናጦስ አባ ሰላማ ከሦስት ጊዜ በላይ ግብጺ እስክንድሪያ ሄዶ ጵጵስና አምጥቶ በኢትዮጵያና በኤርትራ ሃዋርያ ሆኖ እንዲያስተምር እንዲያጠምቅ በእግዚአብሄር መልእክት ተነገረው፡፡ በዚህ መሰረት  ስለአየው ነገር ለነገስታቱ አስረዳቸው ከዚህ በኋላ ጵጵስና እንዲያመጣ መልካም ፍቃዳቸው ስለሆነ ወደ እስክንድርያ ሄደ፡፡  

 

ፍሬምናጦስ እስክንድርያ የደረሰው እለ እስክንድሮስ አትናቴዎስን አስከትሎ ለጉባኤ ኒቅያ በወጣበት ጊዜ ነበርና እስኪመለሱ ድረስ ትምህርተ ቤተክርስቲያንን እየተማረ በትዕግስት መጠበቅ ግድ ሆነበት፡፡ እለ እስክንድሮስ በጉባኤ ኒቅያ በአትናቴዎስ አፈ ጉባኤነት አርዮስን ረትቶ ከተመለሰ በኋላ ወዲያው ስላረፈ በመንበሩ አትናቴዎስ ተተካ፡፡

 

ፍሬምናጦስም የሄደበትን አብይ ጉዳይ ለቅዱስ አትናቴዎስ አቀረበ፡፡  አትናቴዎስም ስለ ኢትዮጵያውያን ሐይማኖት በሚገባ ከተረዳ በኋላ ለፍሬምናጦስ ስርዓተ ቤተክርስቲያንን አስተምሮ ኤጲስ ቆጶስ ዘአክሱም ወዘኩላ ኢትዮጵያ ብሎ በአንብሮተ ዕድ ተሾመ፡፡  በሹመቱም ወቅት ሰላማ የሚል ስም እንዲወጣለት መልአኩ ቅዱስ ዑራኤል ለኢየሩሳሌም ኤጲስ ቆጶስ አባ ቄርሎስ በራእይ ተገልጾ ነግሮታል፡፡

 

ሰላማ ማለት፡ በእግዚአብሔርና በሰው መካከል ሆኖ የሚያስታርቅ ማለት ነው፡፡  በዘመነ ረሃብ ጥጋብ፣ በዘመነ ጦርነት ሰላም የሚሰጥ ማለት ነው፡፡  ብርሃነ ወንጌሉን ለኢትዮጵያውያንና ለኤርትራውያን ስላበሰረ፤ በብርሃነ ትምህርቱ የተደሰቱ በጨለማው ውስጥ ኖረው በእርሱ አማካኝነት ወንጌሉ የበራላቸው ምዕመናን ከሳቴ ብርሃን በማለት ሰይመውታል፡፡  ቅዱስ ያሬድም ዝንቱ ብእሲ መምህርነ ዘተፈነወ ውስተ ምድር ይከስት ብርሃነ ማለትም ብርሃንን ይገልጥልን ዘንድ ወደ አገራችን የተላከ ይህ ሰው መምህራችን ነው ብሎታል፡፡  /መጽ.ድጓ/

 

ሰአል ለነ ሰላማ አቡነ ወመምህርነ እለ ፅልመት ነበርነ ከሰትከ ለነ ብርሃነ ዜናሁ ለመድሃኒነ፤ አባታችንና መምህራችን አቡነ ሰላማ በጨለማ የነበርን ለኛ የክርስቶስ ብርሃነ ወንጌል አበራህልን፡፡ /አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በሰዓታት

 

አባታችን ከተሾመ በኋላ፡

ወንጌልን በስፋት ለህዝቡ የሚያደርሱ፣ የሚያጠምቁና የሚያቆርቡ ካህናትና ዲያቆናትን ሾመ፤

በአብርሃ ወአጽብሐ አማካኝነት ብዙ አብያተ-ክርስቲያናትን አሳነጸ፤

በዘመኑ የኢትዮጵያ ግዛት ወደ ነበሩበት ኑብያ፣ አኑኖ እና መርዌ 5 ቆሞሳትን በመላክ ትምህርተ ወንጌል እንዲሰበክ እና ቤተክርስቲያን እንድትስፋፋ አድርጓል፤

ቅዱሳት መጻሕፍትን ከሱርስት፣ ከእብራይስጥና ከግሪክ ወደ ግዕዝ ቋንቋ እንዲተረጎሙ አድርጓል፤

የሳባውያንን የፊደል አቀማመጥ በመለወጥና ከግራ ወደ ቀኝ የመጻፍንና የማንበብን ዘዴ አስተምሯል፤

350 . ክርስትና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሐይማኖት ሆኖ እንዲታወጅ አድርጓል፤

በአጠቃላይ

መሰረቷ ያልተናወጸ ቤተክርስቲያንን በስብከቱ የመሰረተ፤

ቅድስናው በጥንት አብያተ ክርስቲያናት የተመሰከረለት፤

የወንጌልን ብርሃን በመላው ኢትዮጵያና ኤርትራ ዞሮ ያበራ፤

በክርስቶስ መስቀል የተገኘውን ሰላም ለኢትዮጵያውያንና ለኤርትራውያን ያስተዋወቀ፤

ሐዋርያዊ ግዴታውን በሚገባ የተወጣ፤

በኢየሩሳሌም ላለው ርስታችን በነበረበት ዘመን መፍትሔ ያሰጠ፤

የአርዮስን ትምህርት በመጣበት ቦታ የመለሰ፤

መንበሩን በዓለም አቀፍ እውቅና ያካተተ፤

ለአገሪቱ ጭምር የሥነ ፊደል ሥርዓት የዘረጋ፤

አገራችን በራሷ ቋንቋ መጽሐፍ ቅዱስን እንድታገኝ የተረጎመ፤

ፍጹም ሐዋርያዊ ሕይወት የነበረው ታላቅና ቅዱስ የቤተክርስቲያናችን አባት ነበር፡፡

 

ኣቡነ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን የተባለው ፍሬምናጦስ በኢትዮጵያና በኤርትራ ክርስትና ሓይማኖት እንዲስፋፋ ከሰሜን እስከ ደቡብ ከምዕራብ እስከ ምስራቅ በመውጣትና በመውረድ የሚገባውን ሁሉ ከፈጸመ በኋላ ሐምሌ 26 ቀን ወደ ዘላለማዊ ክብሩ ተሸጋግሮዋል፡፡ 

 ethiopian-bible-in-geez

ይህ ታላቅ አባት የኢትዮጵያውያንና የኤርትራውያን ባለ ውለታ የወንጌልን ፋና ይበልጥ እንዲበራ ያደረገ፡፡ መንበረ ጵጵስና ያስገኘልን ስርዓተ ቤተክርስቲያን ለኢትዮጵያውያንና ለኤርትራውያን የወጠነልን እና አያሌ ቤተክርስቲያን ያሰተከለልን ነውና ዘወትር ልናስበው በዓሉን ልናከብርለት ይገባናል፡፡

 

ይህ ቅዱስ ኣባት አፅሙ ያረፈበት ገዳሙ የሚገኝው ትግራይ ውስጥ በተንቤን እንዳ ኣባ ሰላማ ሲሆን እንዲሁም ኤርትራ ዛግር እና በኣንዳንድ ቦታዎች ካልሆነ በቀር በአብዛኛው የሃገራችን ክፍል ክብረ በዓሉ እምብዛም ትኩር አይሰጠውም፡፡

 

በረከት በጻድቅ ራስ ላይ ነው ምሳ.106 ተብሎ እንደተጻፈው ጻድቁ አባታችን ማር ኅሩይ አቡነ ሰላማ ሙታንን አስነስቷል /የጥርና የሰኔ ገድል/ ጸሐይን ከተፈጥሮ ህግ ውጪ አቁሟል /የነሐሴ ገድል/ የአባይን ወንዝ ከፍሎ ተሻግሯል /የመስከረም ገድል/ በዚህ ዓይነት የተጋድሎ ሂደት 150 ዓመታት መልካም ገድልን ተጋድሏል፡፡  ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር የገባለት ቃል ኪዳን ስምህን የጠራ ዝክርህን የዘከረ ገድልህን ያነበበ ሲነበብ የሰማ ቤተክርስቲያንህ የሰራ ዘቢብ እጣን ጠዋፍ ሻማ ለቤተክርስቲያንህ የሰጠ ልጁን ብስምህ የሰየመ አምኖ ሳይጠራጠር ጸበልህን የተጠመቀ እርኩሳን መናፍስት አይቀርቡትም አስራ አምስት ትውልድም እምርልሃለሁ የሚል ቃል ኪዳን ተቀብሏል፡፡ ይህንን ታሳቢ በማድረግና በእግዚአብሔር ቸርነት በተሰጠው ልዩ ቃልኪዳን መሰረት 21ኛው /ዘመን በስሙ የሚደረጉ ተአምራቶች እንደቀጠሉ ናቸው፡፡ የዚህ ቃልኪዳን ተጠቃሚዎች እንድንሆን አባ ሰላማ በቃል ኪዳኑ እግዚአብሔር በቸርነቱ ይርዳን፡፡

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

መደቦቻችን

No events

የመፅሓፍ ቅዱስ ጥቅስ

readings "  በጌታ የተወደዳችሁ ወንድሞች ሆይ፥ ሁልጊዜ ስለ እናንተ እግዚአብሔርን ልናመሰግን ግድ አለብን፥ እግዚአብሔር በመንፈስ መቀደስ እውነትንም በማመን ለመዳን እንደ በኵራት መርጦአችኋልና"   

              2ኛ ወደ ተሰሎን 2:13

በኣባ ሳሙኤል የቀረቡ መፃህፍትና ቪቺዲዎች

abb 1

ካባቶኣንደበት

stanthony"ለእግዚኣብሄር ከወንድምህ በላይ ውደደው ለወንድምህ ደሞ ከነፍስህ በላይ ውደደው"   ኣባ ይስሓቕ ሶርያዊ

ካባቶች ምክር

stanthony"ኣንዲት የክፋት ቃል ለመልካም ሰው ክፉ ታደርገዋለች፥ ኣንዲት መልካም ቃል ግን ለ ክፉ ሰው መልካም ታደርገዋለች።"    ኣባ መቃርዮስ 

saying fathers

stanthony"If then we have angels, let us be sober, as though we were in the presence of tutors; for there is a demon present also."   John Chryssostom

saying of fathers

stanthony"Let books be your dining table, / And you shall be full of delights. / Let them be your mattress,/And you shall sleep restful nights"   Ephraim the Syrian

 

              በነዚ ላይ በመጫን ይከተሉን

  twitter-logo-circular-OFFfacebThis email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.

adress