christmas star Mahbere Abune Selama- self help association, support those in need, Spiritual gatherings, youth and adult counselling  christmas star

lo 1

                           cross animation small የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ታሪክcross animation small

 

ሀገራችን አስቀድማ ብሉይ ኪዳንን የተቀበለች ከቤተ እስራኤል ቀጥላ በአምልኮተ እግዚአብሔር የታወቀች ሀገር ናት፡፡ በንግስተ ሳባ ኣማካኝነት የብሉይ /የኦሪት/ እምነት ወደ ሀገራችን ገብቷል፡፡ ከንግስተ ሳባ የኢየሩሳሌም ጉብኝት በኋላ ኢትዮጵያና ኤርትራ በመንፈሳዊም ሆነ በማኅበራዊ እድገት በኩል ያገኙት በረከት ብዙ ነው፡፡ እነዚህም

ethiopian-manuscript

 • የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ባለቤት
 • የሥዩማን ካህናት አገልጋይ፤
 • የታቦተ ሕግ መንበር፤
 • የተደራጀ የቤተ ክሀነት ሥርዓት ሀገር ለመሆን በቅተዋል፡፡

 

በኋላም የዓለምን ተሰፋ የፈፀመው መሲሕ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የመሠረተውን የክርስትና እምነት 34 . በግዕዝ ተቀብለዋል፡፡ ከዚህም በኋላ በአቡነ ከሳቴ ብርሃን ሰላማ ፅኑ መሠረት ያለው የክርስትና እምነት 4ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ተሰብኳል፡፡ በዚህ መሠረት የኢትዮጵያና የኤርትራ ቤተ ክርስቲያን በሐዋርያት ነጋሪት መቺነት የወንጌልን ገፈት ቀምሰዋል፡፡ ሕገ ኦሪትን ሳይረሱ፤ ሁለቱን እያጣጣሙ በክርስቶስ ደም የበቀለውን እውነተኛ ትምህርት ነው የሚያስተምሩት፡፡ ወደ ኣንድ ቢሊዮን የሚጠጋ የዓለም ጥቁር ሕዝብ የታሪክ እምብርት የተቋጠረው በዚሁ ነው፡፡

አንድ ታላቅ ሀገርና አንድ ነባር ቤተ ክርስቲያን አጣምሮ የያዘ ታሪክ ያላቸው ሕዝቦች ቢኖሩ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን ነን፡፡ ወንጌልንና ቤተ ክርስቲያንን የያዙ ብሉይ ኪዳንና ቤተ መቅደስ የላቸውም፤ ብሉይ ኪዳንና ቤተመቅደስ የነበራቸውም አዲስ ኪዳንና ቤተ ክርስቲያን የሏቸውም፤  ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን ብልጫችን እዚህ ላይ ነው! ብሉይ ኪዳንና አዲስ ኪዳንን፤ ቤተ መቅደስና ቤተክርስቲያን፤ ትንቢትንና ስብከትን፤ ምሳሌውንና አማናዊውን አስተባብረን ጠብቀን ይዘን መኖራችን ነው፡፡ ይህን ዘመን የማይሽረውን በሰማይም በምድርም በምድርም ፍፁም ዋጋ ያለውን ህልፈትና መለወጥ የማይስማማውን ታሪክ ስላወቁና ስለተረዱ ነው ቀደምት አባቶች ቤተ ክርስቲያናቸውን ከሀገራቸው ያልለዩት፡፡

እኛም ይህን ካመንን የታሪካችንን ባለ ዋጋነት ልንገነዘብ ያስፈልጋል፡፡ እንዲህ ከሆነ የሃይማኖትን ነገር ልናስተምር እንጂ ሊያስተምሩን መሻት የለብንም ኢትዮጵዊ ሆኖ የቤተ ክርስቲያን ያልሆነ አለ ቢባል አይቻልም፡፡ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን በፍፁም ጠላት ሊኖራት አይገባም ከየት የመጣ ኢትዮጵያዊ ነው የሷ ጠላት? ጠላቶች አሏት ቢባል እንኳ በኢትዮጵያ ምድር ያልተወለደ መሆን አለበት፡፡ ይህ ከላይ የገለፅናቸው ዋና  ዋና ርዕስ ጉዳዮች ወደ መጽሐፉ ይዘት ከመግባታችን በፊት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በምድር ሓበሻ ለማስተዋወቅ ያህል የሠፈረ ነው፡፡ በአጠቃላይ

ቅድስት ሀገራችን/ቤተክርስቲያናችን

cross

 • የጥንት ሥልጣኔ ምንጭ፤
 • ኦሪትና ወንጌል በምድሯ ላይ ያስተናገደች፤
 • ለዘመናት ያልተቋረጠ በትረ መንግሥት የተፈራረቀባት፤
 • በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ሴት ንግስት /ሳባ/ ያነገሠች፤
 • በሌላ ዓለም የሌሉ ፍልፍል አብያተ ክርስቲያናትን ያነፀች፤
 • ከአፍሪካ በራሷ ቋንቋና ፊደል የምትመራ ብቸኛ ሀገር፤
 • ጽላተ ሙሴና ግማደ መስቀልን በቅርስነት የያዘች፤
 • በሽታዎችን ሊያጠፉ የሚችሉ ጠበል የሚፈልቅባት፤
 • ጠፍተው የነበሩ መጽሐፍ ሔኖክና ኩፋሌ የተገኙባት፤
 • ኢትዮጵያ 41 ጊዜ በላይ በመጽሐፍ ቅዱስ ስሟ የተገለጠ፤
 • የዓለም ጥቁር ሕዝብ የታሪክ እምብርት የተቋጠረባት፤
 • የቤተ ክርስቲያን መቅረዝ የሆነ ቅዱስ ያሬድን ያስገኘች፤
 • ለመጀመሪያ ጊዜ የመስቀል መልክት ያለው ሳንቲም ያስቀረጸች፤
 • ለነፃነት ተምሳሌ የሆነች፤
 • የባዕድ እጅ ያልዳሰሳቸው፣ ዘመናት ያልሻራቸው የኪዳነ ጥበባት ክምችት ያለባት፤
 • መጽሐፍ ቅዱስን ምንጭ ያደረጉ ባሕል ያላት፡፡

                              ምድረ ሓበሻ ናት፡፡

መደቦቻችን

No events

የመፅሓፍ ቅዱስ ጥቅስ

readings "  በጌታ የተወደዳችሁ ወንድሞች ሆይ፥ ሁልጊዜ ስለ እናንተ እግዚአብሔርን ልናመሰግን ግድ አለብን፥ እግዚአብሔር በመንፈስ መቀደስ እውነትንም በማመን ለመዳን እንደ በኵራት መርጦአችኋልና"   

              2ኛ ወደ ተሰሎን 2:13

በኣባ ሳሙኤል የቀረቡ መፃህፍትና ቪቺዲዎች

abb 1

ካባቶኣንደበት

stanthony"ለእግዚኣብሄር ከወንድምህ በላይ ውደደው ለወንድምህ ደሞ ከነፍስህ በላይ ውደደው"   ኣባ ይስሓቕ ሶርያዊ

ካባቶች ምክር

stanthony"ኣንዲት የክፋት ቃል ለመልካም ሰው ክፉ ታደርገዋለች፥ ኣንዲት መልካም ቃል ግን ለ ክፉ ሰው መልካም ታደርገዋለች።"    ኣባ መቃርዮስ 

saying fathers

stanthony"If then we have angels, let us be sober, as though we were in the presence of tutors; for there is a demon present also."   John Chryssostom

saying of fathers

stanthony"Let books be your dining table, / And you shall be full of delights. / Let them be your mattress,/And you shall sleep restful nights"   Ephraim the Syrian

 

              በነዚ ላይ በመጫን ይከተሉን

  twitter-logo-circular-OFFfacebThis email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.

adress