christmas star Mahbere Abune Selama- self help association, support those in need, Spiritual gatherings, youth and adult counselling  christmas star

lo 1

 

    lovecrossWelcome lovecrossበሰላም ግቡ lovecross

 

 

     Welcome to Saint Selama self help association website. The contents of this website help to develop your spiritual life (develop your relation ship with God) and so we invite you in God Name to benefit your self by using these website. This website provides many helpful contents that is useful for people with matured relationship with God (mature spiritual life), people who are working on developing this relationship, those who are just starting to know God and also those who know nothing about God and religion as well for all of us. Therefore we would love to announce for all people everywhere with gladness to come and see.  

ወደ ማኅበረ ኣቡነ ሰላማ ወብሳይት እንኳን በሰላም ገቡ።በዚ ወብሳይት ውስጥ መንፈሳዊ ሂዎትዎን የሚያግዝና የሚያነቃቃ መደቦች ይዛ ስለቀረብች ተጠቃሚዎች እንድትሆኑ በእግዚኣብሄር ስም እንጠይቃለን። ይህ ዌብሳይት በመንፈሳዊ ሂዎትዎ የጎለመሱ፣ በእድገትና ለውጥ በማምጣት ላይ ያሉ፣ ገና በጅምር ላይ ላሉና የሃይማኖት እውቀት ፈፅሞ የሌላቸ እንዲሁም ለሁላችን የሚያግዝና መንፈሳዊ ሂዎታችን የምያለመልም ልዩ መደቦች ይዛ ቀርባለችና በደስታ ልናበስሮት እንወዳለን። 

 

                                   lllbird

 

'
እንኳን ለታላቁ ኣባታችን ኣቡነ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን ዓመታዊ የእረፍታቸው ክብረ በዓል በሰላም ኣደረሰን። የኣባታችን ኣቡነ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን ጸሎትና በርከት ከማሕበራችን ማሕበር ኣቡነ ሰላማ እና ከሁላችን ሕዝበ ክርስቲያን ጋር ይሁን ኣሜን።

'የቅዱሳኑ ሞት በእግዚአብሔር ፊት የከበረ ነው።'' መዝ 116:15።

የጻድቁ በረከት ከሁላችን ጋር ይሁንና ታላቁ፣ ስመጥሩ አባታችን ጻድቁ አቡነ ሰላማ በ3ኛው መቶ ክፍለ ዘመን መጀመሪያ በ 26 ሕዳር 245ዓ/ም ላይ ከአባቱ ከቅዱስ ምናጦስና ከቅድስት እናቱ ማርያም ሰናይት በጢሮስ /ግሪክ/ ተወለደ፡፡ እድሜው ለትምህርት እንደደረሰ በአካባቢው በነበረው ትምህርት ቤት ውስጥ ሃይማኖታዊ ትምህርቱን በሚገባ ተከታትሎ የተማረ በመልካም ሥነ-ምግባርና አስተዳደግ ተኮትኩቶ ያደገ ደግ አባት ነበር፡፡

አባታችን አቡነ ሰላማ ፍሬምናጦስ በአክሱም በነበረበት ጊዜ የቤተመንግስቱ አማካሪ ብቻ ሳይሆን ቀደም ሲል የኦሪት እምነት በአንድ እግዚአብሄር ማመን እንደነበረ የሚታወቅ ሆኖ የተዋህዶ እምነት ጥምቀትና ክህነትን በሚገባ የሚመሰረትበትና የሚሰፋበት መንገድ ይፈልግ ነበር፡፡ ያን ጊዜ የነበሩት የኢትዮጵያ ክርስቲያኖች ሐይማኖት ብቻ እንጂ ክህነት፣ ቁርባንና የመሳሰሉት የክርስትና ስርዓቶች አልነበራቸውም፡፡ ልዑላኑ /አብርሃና አጽብሐ/ አካለ መጠን ደርሰው የአባታቸውን መንግስት ሲረከቡ ወንድማቸው ኤዴስዮስ ወደ አገሩ ተመልሶ ካህን ሆነ፡፡ ፍሬምናጦስ አባ ሰላማ ከሦስት ጊዜ በላይ ግብጺ እስክንድሪያ ሄዶ ጵጵስና አምጥቶ በኢትዮጵያና በኤርትራ ሃዋርያ ሆኖ እንዲያስተምር እንዲያጠምቅ በእግዚአብሄር መልእክት ተነገረው፡፡ በዚህ መሰረት ስለአየው ነገር ለነገስታቱ አስረዳቸው ከዚህ በኋላ ጵጵስና እንዲያመጣ መልካም ፍቃዳቸው ስለሆነ ወደ እስክንድርያ ሄደ፡፡

ፍሬምናጦስ እስክንድርያ የደረሰው እለ እስክንድሮስ አትናቴዎስን አስከትሎ ለጉባኤ ኒቅያ በወጣበት ጊዜ ነበርና እስኪመለሱ ድረስ ትምህርተ ቤተክርስቲያንን እየተማረ በትዕግስት መጠበቅ ግድ ሆነበት፡፡ እለ እስክንድሮስ በጉባኤ ኒቅያ በአትናቴዎስ አፈ ጉባኤነት አርዮስን ረትቶ ከተመለሰ በኋላ ወዲያው ስላረፈ በመንበሩ አትናቴዎስ ተተካ፡፡ ፍሬምናጦስም የሄደበትን አብይ ጉዳይ ለቅዱስ አትናቴዎስ አቀረበ፡፡ አትናቴዎስም ስለ ኢትዮጵያውያን ሐይማኖት በሚገባ ከተረዳ በኋላ ለፍሬምናጦስ ስርዓተ ቤተክርስቲያንን አስተምሮ ኤጲስ ቆጶስ ዘአክሱም ወዘኩላ ኢትዮጵያ ብሎ በአንብሮተ ዕድ ተሾመ፡፡ በሹመቱም ወቅት ሰላማ የሚል ስም እንዲወጣለት መልአኩ ቅዱስ ዑራኤል ለኢየሩሳሌም ኤጲስ ቆጶስ አባ ቄርሎስ በራእይ ተገልጾ ነግሮታል፡፡

 

13886295 1735612163346625 7262503742334215438 n

 

ሰላማ ማለት፡ በእግዚአብሔርና በሰው መካከል ሆኖ የሚያስታርቅ ማለት ነው፡፡ በዘመነ ረሃብ ጥጋብ፣ በዘመነ ጦርነት ሰላም የሚሰጥ ማለት ነው፡፡ ብርሃነ ወንጌሉን ለኢትዮጵያውያንና ለኤርትራውያን ስላበሰረ፤ በብርሃነ ትምህርቱ የተደሰቱ በጨለማው ውስጥ ኖረው በእርሱ አማካኝነት ወንጌሉ የበራላቸው ምዕመናን ከሳቴ ብርሃን በማለት ሰይመውታል፡፡

''የእግዚአብሔርን ቃል የተናገሩአችሁን ዋኖቻችሁን አስቡ፥ የኑሮአቸውንም ፍሬ እየተመለከታችሁ በእምነታቸው ምሰሉአቸው።'' ዕብራውያን 13:7።
''ቅዱስ አባታችን ኅሩይ ማር አቡነ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን ፍሬምናጦስ''
ታላቁ ኣባታችን ኣቡነ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን - የመጀመሪያ ሃዋርያ ከሰሩዋቸው ስራዎች በከፊል፥
1. የክርስትና ወንጌል ለመጀምሪያ ጊዜ የሰበኩ ከተለያዩ ቋንቋ ወንጌል የተረጎሙ
2. ሙሉ ኢትዮጵያና ኤርትራ ክርስትና ኣጥምቀው ከጨለማ ወደ ብርሃን ያሸጋገሩ
3. በዘመናት ብዛት የማይናወጽ ዶግማና ቀኖና ሰርተው ቤተክርስቲያን የተከሉ 
4. የክርስቶስ ቅዱስ ስጋውንና ክቡር ደሙን እንድንቀበል ያደረጉ 
5. ብዙ ጳጳሳት ፥ ካህናት፥ ዲያቆናት የሾሙልን
6. በገድላቸው በትሩፋታቸው በቅድስናቸው ልዩ የቃል ኪዳን ጸጋ የተሰጣቸው በጥንታውያን ኣባቶች የተመሰከረላቸው፥
7. በቃል ኪዳነቸው ላመኑ የመንግስተ ሰማይ ወራሾች እንዲሆኑ ከኣምላክ ቃል ኪዳን የተሰጣቸው፥ ጻድቅ ሃዋርያዊ ኣባታችን ኅሩይ ማር ኣቡነ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን ፍሬምናጦስ።

ይህ ታላቅ አባት የኢትዮጵያውያንና የኤርትራውያን ባለ ውለታ የወንጌልን ፋና ይበልጥ እንዲበራ ያደረገ፡፡ መንበረ ጵጵስና ያስገኘልን ስርዓተ ቤተክርስቲያን ለኢትዮጵያውያንና ለኤርትራውያን የወጠነልን እና አያሌ ቤተክርስቲያን ያሰተከለልን ነውና ዘወትር ልናስበው በዓሉን ልናከብርለት ይገባናል፡፡ ኣቡነ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን ፍሬምናጦስ በኢትዮጵያና በኤርትራ ክርስትና ሓይማኖት እንዲስፋፋ ከሰሜን እስከ ደቡብ ከምዕራብ እስከ ምስራቅ በመውጣትና በመውረድ የሚገባውን ሁሉ ከፈጸመ በኋላ ሐምሌ 26 ቀን ወደ ዘላለማዊ ክብሩ ተሸጋግሮዋል፡፡

ይህ ቅዱስ ኣባት አፅሙ ያረፈበት ገዳሙ የሚገኝው ትግራይ ውስጥ በተንቤን እንዳ ኣባ ሰላማ ሲሆን እንዲሁም ኤርትራ ዛግር እና በኣንዳንድ ቦታዎች ካልሆነ በቀር በአብዛኛው የሃገራችን ክፍል ክብረ በዓሉ እምብዛም ትኩር አይሰጠውም፡፡

በረከት በጻድቅ ራስ ላይ ነው ምሳ.10፡6 ተብሎ እንደተጻፈው ጻድቁ አባታችን ማር ኅሩይ አቡነ ሰላማ ሙታንን አስነስቷል /የጥርና የሰኔ ገድል/፣ ጸሐይን ከተፈጥሮ ህግ ውጪ አቁሟል /የነሐሴ ገድል/ የአባይን ወንዝ ከፍሎ ተሻግሯል /የመስከረም ገድል/፣ በዚህ ዓይነት የተጋድሎ ሂደት ለ150 ዓመታት መልካም ገድልን ተጋድሏል፡፡ ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር የገባለት ቃል ኪዳን ስምህን የጠራ ዝክርህን የዘከረ ገድልህን ያነበበ ሲነበብ የሰማ ቤተክርስቲያንህ የሰራ ዘቢብ እጣን ጠዋፍ ሻማ ለቤተክርስቲያንህ የሰጠ ልጁን ብስምህ የሰየመ አምኖ ሳይጠራጠር ጸበልህን የተጠመቀ እርኩሳን መናፍስት አይቀርቡትም አስራ አምስት ትውልድም እምርልሃለሁ የሚል ቃል ኪዳን ተቀብሏል፡፡ ይህንን ታሳቢ በማድረግና በእግዚአብሔር ቸርነት በተሰጠው ልዩ ቃልኪዳን መሰረት በ21ኛው ክ/ዘመን በስሙ የሚደረጉ ተአምራቶች እንደቀጠሉ ናቸው፡፡ የዚህ ቃልኪዳን ተጠቃሚዎች እንድንሆን አባ ሰላማ በቃል ኪዳኑ እግዚአብሔር በቸርነቱ ይርዳን፡፡

''ታላቅ ሕዝብም አደርግሃለሁ፥ እባርክሃለሁ፥ ስምህንም አከብረዋለሁ፤ ለበረከትም ሁን፤ 
የሚባርኩህንም እባርካለሁ፥ የሚረግሙህንም እረግማለሁ፤ የምድር ነገዶችም ሁሉ በአንተ ይባረካሉ። '' ዘፍጥረት 12:3። ''የጌታ ዓይኖች ወደ ጻድቃን ናቸውና፥ ጆሮዎቹም ለጸሎታቸው ተከፍተዋል፥'' 1ኛ ጴጥሮስ 3:12።
የአባታችን አቡነ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን ጸሎትና በርከታቸው ከማሕበራችን ማሕበር ኣቡነ ሰላማ እና ከሁላችን ሕዝበ ክርስቲያን ይሁን ኣሜን።

Happy Annual departure feasts of Saint Abune Selama Frumentius. The blessing of the first Arch Bishop of Ethiopia and Eritrea Apostle Saint Abune Selama Kesate Brhan be with Our association & with all orthodox tewahdo Christians.
"For though ye have ten thousand instructors in Christ, yet have ye not many fathers: for in Christ Jesus I have begotten you through the gospel." 1co.4:15
The Blessing of The first Ethiopia and Eritrea Apostle Saint Abune Selama be with Our association and with all Christians. Amen.

 

 

13903326 1735610186680156 5954157456861472493 n

 

 

''እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ። በተራራ ላይ ያለች ከተማ ልትሰወር አይቻላትም።'' ማቴዎስ 5:14

+++እንኳን ለቅዱሳን ሃዋርያት ጴጥሮስ ወጳውሎስ ሰማዕትነት የተቀበሉበት ዓመታዊ ክብረ በዓል እና የኣባታችን ኣቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ወርሃዊ የእረፍታቸው በዓል በሰላም ኣደረሰን። የቅዱሳን ሃዋርያት ጴጥሮስ ወጳውሎስ እና የኣባታችን ኣቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ጸሎት እና በረኸት ከማሕበራችንና ከሁላችን ህዝበ ክርስትያን ጋር ይሁን ኣሜን።+++

''የልዑሉ ቅዱሳን መንግሥቱን ይወስዳሉ፥ እስከ ዘላለም ዓለምም መንግሥቱን ይወርሳሉ።'' ዳንኤል 7:18:: ''የጌታ ዓይኖች ወደ ጻድቃን ናቸውና፥ ጆሮዎቹም ለጸሎታቸው ተከፍተዋል፥'' 1ኛ ጴጥሮስ 3:12

13669804 1725973517643823 2018725833689175228 n 

 

'For the eyes of the Lord are on the upright, and his ears are open to their prayers: '' 1 Peter 3:12

Happy Annual feast of Saint Apostle Peter & Paul and monthly feast of Saint Abune Gebre Menfes Kudus, The Blessing of Saint Apostle Peter, Saint Paul and Saint Abune Gebre Menfes Kudus be with Our association and with all Christians. Amen.
''The saints of the Most High will take the kingdom, and it will be theirs for ever, even for ever and ever.'' Daniel 7:18

13615153 1725973467643828 8614496136681468275 n

 

ማሕበር ኣቡነ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን ኣብ ቅድስት ሃገር እየሩሳሌም ንማሕበር ኣቡነ ሰላማ ኣባላትን ንክልኩም ሕዝበ ክርስቲያን እንዃዕ ናብ ጾመ ጽጌ ናይ እምቤታችን ስደታ ንሓስበሉ ግዜ ኣብጸሓና እናበልና ናይ ኣባ ሳሙኤል ወልደ ሰላማ ስብከት ቁጽሪ 9 ክፍሊ 1 "ነፍሲ ወከፍ ከምቲ እግዚኣብሔር ዝዓደሎ ነፍሲ ወከፍውን ከምቲ ኣምላክ ዝጸውዖ ኮይኑ ይመላለስ" 1ይ ቆሮ7፤17 ዝብል ስብከት ብኣባ ሳሙኤል ወልደ ሰላማ ተዳልዩ ቀሪቡልኩም ኣሎ ንባዓልኩም ተጠቂምኩም ንካላኦት ሼር ብምግባር በረኸት ተሳተፉ፤ ጥቅምቲ 10/2006 ዓ.ም.ግ

 

                        

 

ማሕበር ኣቡነ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን ኣብ ቅድስት ሃገር እየሩሳሌም ንማሕበር ኣቡነ ሰላማ ኣባላትን ንክልኩም ሕዝበ ክርስቲያን እንዃዕ ናብ ጾመ ጽጌ ናይ እምቤታችን ስደታ ንሓስበሉ ግዜ ኣብጸሓና እናበልና ናይ ኣባ ሳሙኤል ወልደ ሰላማ ስብከት ቁጽሪ 9 ክፍሊ 2

 

                          

 

 

               product

ኣቡነ ሰላማ

 

Be aware

 

Dear all saint Selama self help association website users we thank God that He wills this website to give you this service and we thank Saint Selama for his intercession and prayers. We would love to warn you that there are websites, facebooks and other media channel that uses this associations name but that speaks evil of the association. Therefore be aware and don’t be deceived. 

 

      weekly Programs

 

jesus sermon on the mount buttons-p145807933072694819en88u 325Satuarday
14:00 -20:00   spiritual gathering(sermon and hymns)
20:00 -21:30  instructions of using holy water
Sanduy 
20:00 -22:30   spiritual gathering(sermon and hymns)
13:00 -17:00   Councling 
Monday
14:00 -16:30 Councling    
20:00-21:30 bible study courses 
Tuesday 
10:00 -12:00   Councling 
15:00 -14:30   Councling 
Wednesday 
10:00 -12:00   Councling 
Friday 
19:00 -23:00   spiritual gathering(sermon and hymns)

 

      ሳምንታዊ መደቦች

 

jesus sermon on the mount buttons-p145807933072694819en88u 325ቀዳሜ
14:00 -20:00   ጉባኤ
20:00 -21:30  የፀበል ኣጠቃቀም
እሁድ
20:00 -22:30   ጉባኤ
13:00 -17:00   የግል ምክር
ሰኞ
14:00 -16:30 የግል ምክር   
20:00-21:30 መንፈሳዌ ኮርስ
ማክሰኞ
10:00 -12:00   የግል ምክር
15:00 -14:30   የግል ምክር
ሓሙስ
10:00 -12:00   የግል ምክር
ኣርብ
19:00 -23:00   ጉባኤ

 

        

 

                     

መደቦቻችን

No events

የመፅሓፍ ቅዱስ ጥቅስ

readings "  በጌታ የተወደዳችሁ ወንድሞች ሆይ፥ ሁልጊዜ ስለ እናንተ እግዚአብሔርን ልናመሰግን ግድ አለብን፥ እግዚአብሔር በመንፈስ መቀደስ እውነትንም በማመን ለመዳን እንደ በኵራት መርጦአችኋልና"   

              2ኛ ወደ ተሰሎን 2:13

በኣባ ሳሙኤል የቀረቡ መፃህፍትና ቪቺዲዎች

abb 1

ሃሳብዎን ይግለፅሉን

latest Video/የቅርቡ ቪድዮ

ካባቶኣንደበት

stanthony"ለእግዚኣብሄር ከወንድምህ በላይ ውደደው ለወንድምህ ደሞ ከነፍስህ በላይ ውደደው"   ኣባ ይስሓቕ ሶርያዊ

ካባቶች ምክር

stanthony"ኣንዲት የክፋት ቃል ለመልካም ሰው ክፉ ታደርገዋለች፥ ኣንዲት መልካም ቃል ግን ለ ክፉ ሰው መልካም ታደርገዋለች።"    ኣባ መቃርዮስ 

saying fathers

stanthony"If then we have angels, let us be sober, as though we were in the presence of tutors; for there is a demon present also."   John Chryssostom

saying of fathers

stanthony"Let books be your dining table, / And you shall be full of delights. / Let them be your mattress,/And you shall sleep restful nights"   Ephraim the Syrian

 

              በነዚ ላይ በመጫን ይከተሉን

  twitter-logo-circular-OFFfacebThis email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.

adress